Fana: At a Speed of Life!

የጋና ካቢኔ ብሪክስን ለመቀላቀል ጥያቄ ማቅረብ የሚያስችል ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋና ካቢኔ ብሪክስን ለመቀላቀል ጥያቄ ማቅረብ የሚያስችል ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋና የብሪክስ አባል እንድትሆን ቀደም ሲል በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ሃሳብ ቀርቦ እንደነበር በማስታወስ የፕሬዚዳንቱ ሃሳብ በካቢኔ መጽደቁን አመልክቷል፡፡

ውሳኔው የጋናን ዓለም አቀፍ አጋርነቶች ለማብዛትና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ልማት ተጨማሪ ዕድሎችን ለመፍጠር ያለመ ስለመሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

የጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሙኤል ኡኩዜቶ አብላካዋ÷ በቀጣይ ሀገራቸው የብሪክስ የልማት በየነ መንግሥታት ድርጅትን ለመቀላቀል ይፋዊ ደብዳቤ እንድምታቀርብ ጠቁመዋል፡፡

የጋና የብሪክስ አባልነት ከአንድ ህብረት ወደ ሌላ የመዘዋወር ሳይሆን አሁን ካሏት አጋሮቿ በተጨማሪ ከሌሎች ትብብሮች ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጋና የዓለም ባንክ፣ የአይ ኤም ኤፍ እና የአፍሪካ የጋራ የፋይናንስ ተቋማት መስራች ሀገር መሆኗን ጠቁመው፤ ጋና የብሪክስ ምክር ቤት ከሆነች ተጨማሪ የልማት እድሎች እንደሚፈጠሩላት አመላክተዋል፡፡

ጋና እንደ ቻይና፣ ብራዚል እና ህንድ ካሉ የብሪክስ አባል ሀገራት ጋር ጠንካራ የንግድ ግንኙነት እንዳላት ጠቅሰው፤ የጋና የብሪክስ አባልነት የንግድ ግንኙነቱን የበለጠ ያሳድገዋል ማለታቸውን ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.