Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ተርሚናሎች እና መስመሮች ለውጥ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ የተገነቡት አዲስ ዘመናዊ የህዝብ ትራንስፖርት ተርሚናሎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።

በዚህም የትራንስፖርት ተርሚናሎች እና መስመሮች ላይ ለውጥ እና ማስተካከያ ተደርጓል።

በማስተካከያው መሰረትም ቀድሞ ከነበረው የካ ሾላ ተርሚናል አራት የታክሲ መስመሮች ወደ አዲሱ የመገናኛ ተርሚናል (የካ ክፍለ ከተማ አጠገብ) ተዛውረው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ከአዲሱ የመገናኛ ተርሚናል የሚነሱ የታክሲ መስመሮች፡

1.      መገናኛ — ሽሮሜዳ

2.      መገናኛ — አውቶብስ ተራ

3.      መገናኛ — ፒያሳ

4.      መገናኛ — ስድስት ኪሎ

በሌላ በኩል በሾላ ተርሚናል ውስጥ የነበረው የፈረንሳይ የታክሲ መስመር በነበረበት ቦታ ላይ አገልግሎቱን እንዲቀጥል ተደርጓል።

በአዲሱ የመገናኛ ተርሚናል ሁለት የአውቶብስ መስመሮች ስራ የጀመሩ ሲሆን፣ እነሱም ቁጥር 80 (ከመገናኛ – ሽሮሜዳ) እና ቁጥር 64 (ከመገናኛ – ፈረንሳይ ጉራራ) በመሆን አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።

የተርሚናል ለውጥ የተደረገበት ሌላኛው ስፍራ አራት ኪሎ ሲሆን ቀድሞ በገበያውና በመኪና ማቆሚያው ጎን ይነሱ የነበሩ የታክሲ መስመሮች ሙሉ በሙሉ ወደ ግንፍሌ ተርሚናል ተዛውረው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.