በስልጣን ጥም የተጋረደ እውነት፤ የህገ ወጡ ህወሓት የእልቂት አዙሪት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ህገ ወጡ የህወሓት ቡድን ለዓመታት የተከተለው ሰላም ጠል የፖለቲካ መስመር የትግራይን ህዝብ ለሌላ ዙር መከራና ግጭት የሚዳርግ አደገኛ አካሄድ ነው።
ድርጅቱ ከተጋረጠበት የህልውና አደጋ እና የህጋዊነት ቀውስ ለመውጣት የሚያደርገው የቀቢጸ ተስፋ ጥረት፣ የሰላም መንገዶችን ከመከተል ይልቅ ሀገር አፍራሽ እና ጸረ ህዝብ ተግባርን አጠናክሮ ቀጥሎበታል።
ይህ የጥፋት ኃይል የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግሥት እንዲሁም ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ሰላምን ለማስፈን ያቀረቧቸውን ጥሪዎች እንዲሁም የተፈረሙ ስምምነቶችን በሙሉ በመጣስ በግልጽ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ነው።
በየጊዜው የሚፈጸሙ ጸረ ሰላም ድርጊቶች፣ ሉዓላዊነትን እና የህዝቦችን አንድነትን የሚሸረሽሩ እንቅስቃሴዎች፣ የቡድኑን የአጥፊነት ዓላማ በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው።
በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ እንዲረጋገጥ የተዋቀረውን ህጋዊ ጊዜያዊ አስተዳደር በኃይል በማፍረስ የቡድኑን ህገወጥነትና ጸረ ሰላም አካሄድ ቁልጭ አድርጎ ያሳዬ ነው።
የቡድኑ የፕሪቶሪያውን ዘላቂ የግጭት ማቆም ስምምነትን በመጣስ በክልሉ ያለውን አስተዳደራዊ መዋቅር ያፈረሰና የትግራይን ህዝብ በግጭት አዙሪት ውስጥ ለማኖር ከውጭ ኃይሎች ጋር ጭምር እየሰራ ይገኛል፡፡
ህገ ወጡ ህወሓት የራሱን ጠባብ ቡድናዊ ፍላጎት ለማስጠበቅ ሲል ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ህብረት በመፍጠርም ባንዳዊ ተግባር ላይ ተጠምዷል።
የሀገርን ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅምን አደጋ ላይ የሚጥሉ እርምጃዎችን እየወሰደ የሚገኘው ይህ የባንዳ ስብስብ፣ ከሀገር ህልውና እና ከህዝብ ጥቅም በተቃራኒ መቆሙ በግልፅ እየታዬ ነው።
ይህ ህገ ወጥ ቡድን ከጥንተ ስሪቱም ጀምሮ በጸረ ህዝብነቱና ሀገር አፍራሽነቱ የሚታወቅው ይህ የጥፋት ቡድን ዛሬም በጸረ ልማት እና ጸረ ህዝብ ተግባሩ ቀጥሎበታል።
የትግራይ ህዝብ የሰላም፣ የልማት እና የደህንነት ፍላጎት በጦርነት አባዜ እና በፖለቲካዊ ቁማር ሊደናቀፍ አይገባም። በመሆኑም ይህን አደገኛ አካሄድ በማስቆም፣ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እና የትግራይን ህዝብ ከቀጣይ ግጭት ማዳን የወቅቱ አማራጭ የሌለው ተልዕኮ እና ሀገራዊ ኃላፊነት ነው።
የሀገራችንን ሉዓላዊነትና የብልፅግና ጉዟችን ለማፋጠን መላው ኢትዮጵያዊያን የዚህን የጥፋት ኃይል በአንድነት ሆኖ መታል ይገባል፡፡
በመልካም ፈቃዱ