Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞዋ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ናቪ ፒላይ የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞዋ የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ኮሚሽነር ናቪ ፒላይ የ2026ቱን የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸንፈዋል፡፡

የሰላም ኖቤል ኮሚቴ ሊቀመንበር ጆርጌን ዋተም ፍሪድነስ በዛሬው ዕለት እንዳስታወቁት÷ ናቪ ፒላይ ለሰብዓዊ መብት መከበር ላሳዩት ቁርጠኝነት እና ድፍረት የ2026ቱ የሰላም ኖቤል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ግለሰቧ ሁሉን አቀፍ የሆነ ዓለም አቀፍ የሕግ ሥርዓት እንዲኖር ለማድረግ ጠንካራ አመራር ሲሰጡ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

የደቡብ አፍሪካ እና ሕንድ ዜገነት ያላቸው ናቫኔተም ወይም ናቪ ፒላይ ከ2008 እስከ 2014 ድረስ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በመሆን የመሩ የሕግ ባለሙያ ናቸው፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.