Fana: At a Speed of Life!

ሊቨርፑል ከማንቼስተር ሲቲ፡ ተጠባቂው የአንፊልድ ፍልሚያ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ6ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ወደ አንፊልድ አቅንቶ ሊቨርፑልን የሚገጥምበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ምሽት 12፡30 ሰዓት በአንፊልድ በሚደረገው ጨዋታ ሊቨርፑል ወደ ዋንጫ ፉክክሩ ለመመለስ ማንቼስተር ሲቲ ደግሞ መሪነቱን ለማስጠበቅ ወደ ሜዳ ይገባሉ፡፡

ባለፉት 26 ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ ወደ አንፊልድ ተጉዞ ሁለት ጊዜ ሊቨርፑል ደግሞ 15 ጊዜ ሲያሸንፍ 9 ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት አጠናቅዋል፡፡

የፕሪሚየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ማንቼስተር ሲቲ በ15 ነጥብ እየመራ የሚገኝ ሲሆን÷ ሊቨርፑል ደግሞ በ9 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በሌላ በኩል ቀን 10 ሰዓት ላይ ክሪስታል ፓላስ ከኖቲንግሃም ፎረስት እንዲሁም ሃል ሲቲ ከኤቨርተን የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.