የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች 19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አከበሩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ከኢትዮጽያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻህፍት አገልግሎት ሰራተኞች ጋር በመሆን 19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አክብረዋል፡፡
19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ሃሳብ በዛሬው ዕለት በመላው ኢትዮጵያ እየተከበረ ይገኛል፡፡
የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቸሩጌታ ገነነ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ትናንት አባቶቻችን በከፈሉት መስዋትዕነት ያልተደፈረች ሀገር ወርሰናል፡፡
የሠንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር ትናንት መስዋዕትነት የከፈሉትንና ዛሬም ለኢትዮጵያ አንድነት የሚዋደቁትን የሰላምና የጸጥታ አካላትን በማክበር ሊሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡