Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የምትታወቀው ነፃነቷንና ሉዓላዊነቷን በተባበረ ክንዷ ከወራሪ በመጠበቅ ነው -ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የምትታወቀው ነፃነቷንና ሉዓላዊነቷን በጽኑና በተባበረ ክንዷ ከወራሪ በመጠበቅ ነው አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ።

ፕሬዚዳንቱ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ፥ ኢትዮጵያ የምትታወቀው ነፃነቷንና ሉዓላዊነቷን በጽኑና በተባበረ ክንዷ ከወራሪ በመጠበቅ ነው ፤ የዚህም ምስጢሩ ሕዝቦቿ ለሰንደቅ ዓላማቸው ያላቸው ጥልቅ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜት ነው ብለዋል።

ይህ አርማችን፣ በመላው ጥቁር ሕዝብ ዘንድ የነፃነት፣ እኩልነትና የፅናት ተምሳሌት በመሆኑ በርካታ ሀገራት ቀለማቱን የሰንደቃቸው አካል አድርገው ወስደውታል ለዚህም ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው ሲሉም አመልክተዋል።

#ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.