የፋና 80 ምዕራፍ 5 የፍጻሜ ውድድር
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት፣ 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ10 ተከታታይ ሳምንታት 16 የዳንስ ቡድኖችን ሲያሳትፍ የነበረው ፋና 80 የዳንስ ውድድር ምዕራፍ 5 ወደ በመጪው እሁድ ፍጻሜው ያገኛል።
ለፍጻሜ የደረሱት ዮዳሄ እና አፍሮ የተሰኙ ቡድኖች በባሕል እንዲሁም ቲ ተስፋ እና ዘውድ በዘመናዊ ዳንስ የምዕራፉ ኮከብ ለመሆን የዳንስ ጥበብ ስራቸውን ያቀርባሉ።
በምዕራፍ 5 በተደረጉት የዙር ውድድሮች ቡድኖቹ የፈጠራ ችሎታቸውን፣ የመድረክ ብቃታቸውንና የውዝዋዜ እና የዳንስ አቅማቸውን አሳይተዋል።
በምዕራፍ 5 ፍጻሜ ሃሳብን በዳንስና ውዝዋዜ ጥበብ ስጋ አላብሰው የላቀ አቅማቸውን የሚያሳዩበት ታላቅ ፍልሚያ እንደሚሆን ይጠበቃል።
የምዕራፉ ኮከብ ለመሆንና የተዘጋጀውን የግማሽ ሚሊየን ብር ሽልማት ለመከፋፈል አጓጊ ፉክክር ያደርጋሉ።
ማን የምዕራፍ 5 ኮከብ ይሆናል?
አጓጊ ፉክክር የሚታይበትን ይህንን አይረሴ እና አስደናቂ የምዕራፍ 5 የፍፃሜ መድረክ በመጪው እሁድ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሁለቱም የቴሌቪዥን ቻናሎች ይጠብቁን።
በብርኽቲ ማህተመ