ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ያላትን ዝግጁነት ለካፍ አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2029 የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ያደረገችውን ዝግጅት በተመለከተ ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ልዑካን ቡድን ገለጻ አድርጋለች፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄና ዝግጅት ለመገምገም የተሰየመው ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል።
የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) ከልዑካን ቡድኑ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ እያደረገች ያለውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እንዲሁም የውድድሩን አስፈላጊነት በተመለከተ ለልዑካን ቡድን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የካፍ ልዑካን በበኩላቸው በተደረገላቸው አቀባበልና ገለጻ መደሰታቸውን ገልፀው፤ ለአምስት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታ የኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት በተመለከተ ምልከታዎችን እንደሚያመርጉ የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡