Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባን የስፖርት ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የሁላችንም ተሳትፎ ወሳኝ ነው – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባን የስፖርት ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የሁላችንም ተሳትፎ ወሳኝ ነው አሉ የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

16ኛው የአዲስ አበባ ስፖርት ምክር ቤት ጉባዔ እየተካሄደ ነው።

ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት÷ ስፖርት ጤናችንን ያሻሽላል፣ አንድነታችንን ያጠናክራል እንዲሁም የወዳጅነት ድልድይ ይሆናል ብለዋል።

ስፖርት ለከተማዋ የቱሪዝምና የኢኮኖሚ ዕድገት ዕድሎችን ይፈጥራል ያሉት ከንቲባዋ÷ አዲስ አበባን የስፖርት ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የሁሉም ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች በእኩልነት እናሳትፍ፤ ተደራሽና ጥራት ያላቸውን የስፖርት መሠረተ ልማቶች እናስፋፋ፣ እንንከባከብ፣ በኃላፊነት እንጠቀም ሲሉም አስገንዝበዋል።

የስፖርት ዕድገት የሁሉም የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመው÷ ዛሬ በስፖርት በመሳተፍ፣ ወጣቶቻችንን በመደገፍና የስፖርት መሠረተ ልማቶቻችንን በመንከባከብ የተሻለች አዲስ አበባን እንገንባ ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.