የሲዳማ ክልል የ2019 በጀት 55 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል የ2019 በጀት 55 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸድቋል።
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 7ኛ ምርጫ ዙር 1ኛ ሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡
የበጀት ዕቅዱን ለምክርቤቱ ያቀረቡት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ዳዊት ሀዬሶ (ዶ/ር) በጀቱ በዋናነት በክልሉ በድህነት ቅነሳ፣ በመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ በዘላቂ የልማት ግቦች እና በተያያዥ ቁልፍ ተግባራት ላይ የሚውል መሆኑን አስረድተዋል።
የቀረበውን በጀት የምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምጽ ማጽደቃቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡