Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ሲቲ ከአርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 6 ከፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ኢፕስዊች ታውንን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የማንቼስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ብራውት ሃላንድ (2) እና ፊል ፎደን አስቆጥረዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ሲቲ ከተከታዩ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 6 ከፍ አድርጓል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ በሊጉ እስካሁን ያደረጋቸውን ሁሉንም 7 ጨዋታዎች አሸንፏል፡፡
በሌላ የሊጉ ጨዋታ ሊቨርፑል ብሬንትፎርድን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ቪክቶር ሙኖዝ እና አሌክሳንደር አይዛክ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ፉልሃም ሃል ሲቲን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፏል፡፡
አስቀድሞ በተደረገ የሊጉ ጨዋታ ቼልሲ ኤቨርተንን ፔድሮ ኔቶ ባስቆጠራቸው ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወቃል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ኒውካስል ዩናይትድ ከአስቶን ቪላ ይገናኛሉ፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.