Fana: At a Speed of Life!

“የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ለሚገኘው 119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 15 ቀን 2019 ዓ.ም
ጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ.ም ዓጼ ምኒልክ የጦር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ያቋቋሙበት እና ፊት አውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴን የጦር ሚኒስትር አድርገው የሾሙበት ዕለት ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በዚህ ታሪካዊ ዕለት በየዓመቱ ጥቅምት 15 መከበሩ ቀደምት ጀግኖችን ሞዴል ያደረገ፣ ከቀደምቶች ታሪክ የሚማር እና የሀገር አለኝታ ሆኖ ሀገርን ለትውልድ የሚያወርስ ሠራዊት ለመገንባት ያለመ ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለ119 ዓመታት ለሠው ሠራሽና ተፈጥሯዊ መሠናክሎች ሳይበገር ባህር ተሻግሮ የመጣንም ጠላት ሆነ የውስጥ ችግር ፈጣሪ ባንዳን እንደ አመጣጡ በመመለስ ለሀገሩና ለህዝቡ ሠላም፣ ለሠንደቅ ዓላማው ክብር እና ለሉዓላዊነቱ መከበር መስዋዕትነት እስከመክፈል በዘለቀ ጀግንነቱ አደራውን እየተወጣ የሚገኝ የህዝብ ልጅ ነው።
ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን በተለያየ መንገድ ለመጉዳት ሲያስቡ የኖሩ ያልተሳካላቸው ታሪካዊ ጠላቶቻችን አሁን ላይም ኢትዮጵያ እንዳታድግ ህዝቦቿ ማልማት እንዳይችሉ ሴራዎችን ሲሸረቡ ቢስትዋሉም ክብር ለመከላከያ ሠራዊት ይሁንና ኢትዮጵያንና ብሄራዊ ጥቅሟን የማሥከበር ተልዕኮውን በጀግንነት እየተወጣ ይገኛል።
የሠራዊት ቀንን ስናከብር አገራችንን የሚፈትኑ የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን ፍላጎት በመረዳት እንደ ሠራዊት ያለንን ወታደራዊ ዝግጁነት በማጠናከርንና ለማንኛውም ተልዕኮ ዝግጁ በመሆን ብሎም ተልዕኮን ለመወጣት በሚያሥችል ቁመና ላይ በመገኘትም ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገራችንን ሉዓላዊነት፣ የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ በፅናት የቆመ በማይታጠፍ ክንዱ የኢትዮጵያ የማይበገር ጋሻና መከታ በመሆኑ ዕለቱን ስናከብር፣ ሀገር የሠጠቻቸውን አደራ ተቀብለው ለሀገር ክብርና ለሰንደቅ ዓላማቸው ከፍታ መስዋዕት ከፍለው ሀገር ያፀኑ ጀግኖችን በማሰብም ጭምር ነው።
በፈተናዎች ውስጥ ሆኖ ራሱን እያሳደገና ጠላቱን እየመከተ አቅሙን እያጎለበተ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገሩን ብቻ ሳይሆን የቀጠናውን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ የሚያስችል ሁለንተናዊ ዝግጁነት እየገነባ መሆኑም እሙን ነው።
መከላከያ ከለውጡ ማግስት ወዲህ በተቋማዊ ማሻሻያዎች በርካታ ውጤቶችን አሥመዝግቧል። በዘመናዊ ትጥቅ፣ በላቀ ቴክኖሎጂና በፅኑ ወታደራዊ ስነ-ምግባር የታነፀ ሠራዊት ገንብቷል፤ ትጥቁም የዛኑ ያህል ዘምኗል። ይህ ተቋማዊ የዕድገት ግስጋሴ የሀገር ትልቅ ተስፋ ሆኖ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጠል ዕምነታችን ከፍ ያለ ነው።
“የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘው የዘንድሮው 119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀንን ስናከብር መላው ህዝባችን ለመከላከያ ሠራዊት ያለውን ድጋፍና ደጀንነት እንደወትሮው ሁሉ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በማመን ነውና በተለያዬ መንገድ ለመከላከያ ሠራዊት ክብር ለሚሠጡ ሁሉ ያለንን ክብር በዚሁ ዕለት ለመግለፅ እንወዳለን።
ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሀገር ውስጥም በሠላም ማሥከበር ተልዕኮ ለምትገኙ የመከላከያ ሠራዊት አመራርና አባላት እንኳን ለ119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን በዓል በሠላም አደረሳችሁ መልካም በዓል!!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.