Fana: At a Speed of Life!

የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ዳር ድንበር ከማስከበር ባሻገር በልማትም በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል – ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ዳር ድንበር ከማስከበር ባሻገር በልማትም በንቃት እየተሳተፈ ነው አሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ።
የምስራቅ ዕዝ ከሀረሪ ክልል መንግሥትና ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር ያስገነባውን ዘመናዊ የእጅ ኳስ ሜዳ በርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።
በዚህ ወቅትም ርዕሰ መስተዳድሩ ኦርዲን በድሪ እንደተናገሩት÷ የመደመር መንግሥት በሁሉም ዘርፎች አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ ነው።
የሀገር መከላከያ ሠራዊትም የሀገርን ዳር ድንበር ከማስከበር በተጨማሪ በሚከናወኑ የልማት ስራዎች የበኩሉን ሚና እየተወጣ መሆኑን ጠቁመዋል።
ምስራቅ ዕዝ የሀረርን ገናናነት እውን በማድረግ ሂደት በተለይም በኮሪደር ልማት ሥራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈ መሆኑን ገልጸው በተሻለ ፍጥነትና ጥራት የተጠናቀቀው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ አንዱ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀነራል ፍቃዱ ፀጋዬ በበኩላቸው÷ ሠራዊቱ የተጣለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት ከመወጣት ባሻገር የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
የመንግሥትና የግል ተቋማት እና ህብረተሰቡን በማሳተፍ እውን የተደረገው ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራም በሰራዊቱና በህዝቡ መካከል ያለውን ትስስር የበለጠ ያጠናክራል ነው ያሉት።
በተስፋዬ ኃይሉ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.