Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካዊ ችግሮች – የሩሲያና አፍሪካ የጎለበተ አጋርነት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አፍሪካ በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች አህጉር ናት፤ ነገር ግን ለዘመናት ሀብቶቿን ሌሎች ቅኝ ገዢዎች ሲጠቀሙበት ተመልካች ሆና ቆይታለች፡፡

አፍሪካውያን ከቅኝ ግዛት ቀንበር ከተላቀቁ በኋላ የራስን ችግር በራስ የመፍታት ፍላጎታቸውን ለማሳካት የጋራ ትብብራቸውንም ለማጠንከር እንደ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አፍሪካ ህብረት) ያሉ ተቋማትን መስርተዋል፡፡

አፍሪካውያን የአህጉሪቱን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ ችግሮቻቸውን በቤታቸው መፍትሄ ለመስጠት፣ በምግብ ራስን የመቻል አጀንዳን ለማሳካት በመሻት አፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካዊ ችግሮች መርህን እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡

የዚህ መርህ ዓላማ የፖለቲካ ችግሮችን እንዲሁም የልማት እቅዶቻቸውን የሌሎች ጣልቃ ገብነት ሳይኖርባቸው በአፍሪካውያን እውቀት መፍትሄ ማግኘት እንዲችሉ ያለመ ነው፡፡

ይህም አፍሪካውያን የራሳቸውን አቅም የሚያጠናክሩበት ሂደት የሌሎችን ጫና ለመቋቋምና መብታቸውን ለማስከበር አቅማቸውን እንዲያጠናክሩ ያግዛል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ሩሲያ ግንባር ቀደም አጋር ሆና ትታያለች፤ ሩሲያ የአፍሪካ ሀገራት ራሳቸውን ለመቻልና የሌሎችን ጣልቃ ገብነት ለማስቀረት የሚያደርጉትነ ጥረት ከሚደግፉ ሀገራት መካከል ነች፡፡

ሀገራት አቅማቸውን በማጠናከር የሌሎችን ጫና መቋቋምና የነርሱን ጥቅም ከግምት ያስገቡ ውሳኔዎችን ማስቀረት እንደሚችሉም በማመን የተለያዩ ትብብሮችን ታደርጋለች፡፡

አፍሪካውያን ከሩሲያ ጋር ያላቸው ግንኙነት ዛሬ በድንገት የመጣ አይደለም ይልቁን በታሪክ የተሳሰረ፣ በፍጥነት እያደገና እየተጠናከረ የመጣ እንጂ።

ሩሲያ ከአፍካውያን ጋር የምታደርገው ግንኙነት በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ ሲሆን፤ ሁሉን አቀፍ በሚባል ደረጃ በርካታ ትብብሮችን ያደርጋሉ፡፡

በጂኦፖለቲካ፣ በምግብ ዋስትና፣ በንግድ፣ በፀጥታ፣ በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ እንዲሁም በኃይልና በመሳሰሉት ዘርፎች ትብብርን ያደርጋሉ፡፡

ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ከምታደርገው የሁለትዮሽ ግንኙነት በተጨማሪ እንደ ብሪክስ ባሉ የባለብዙ ወገን ግንኙነቶችም ተሳስራለች፡፡

በሩሲያ ሞስኮ ዛሬ እና ነገ የሚካሄደው 3ኛው የሩሲያ አፍሪካ ጉባኤ የዚህ ትብብር መገለጫ ነው፡፡

በቤተልሔም ግርማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.