ክርስቲያኖ ሮናልዶ የምንጊዜም ምርጥ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በፈረንጆቹ 2008 ያሳካው የባሎንዶር ሽልማት የምንጊዜም ምርጡ ተብሎ ተመርጧል፡፡
በፍራንስ ፉትቦል የተዘጋጀው የምንጊዜም ምርጡ ባሎንዶር የደጋፊዎች ምርጫ ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡
በዚህም መሰረት ክርስቲያኖ ሮናልዶ በፈረንጆቹ 2008 ያሸነፈው ባሎንዶር በእግር ኳስ ተመልካቾች በተሰጠ ድምጽ የምንጊዜም ምርጥ ባሎንዶር ተብሎ መመረጥ ችሏል፡፡
ሊዮኔል ሜሲ በፈረንጆቹ 2012 ያሸነፈው ባሎንዶር በተመልካቾች ምርጫ የምንጊዜም 2ኛ ደረጃን ሲይዝ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2017 ያሳካው ባሎንዶር ደግሞ 3ኛ ደረጃ መያዙን ማርካ ዘግቧል፡፡
በመልካም ፈቃዱ