በደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልገሎት ሥራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልገሎትን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በከተማዋ ፈጣን እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት የተገነባ ነው፡፡
የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ በርካታ ተቋማትን እና በርካታ አገልግሎቶችን በአንድ ጊዜ መስጠት የሚያስችል መሆኑም ተመላክቷል።
በአማራ ክልል ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት እየተገነቡ ለአገልግሎት እየበቁ ይገኛሉ።