Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሳምንቱ መጨረሻ በዓለም አቀፍ መድረክ አሸንፈዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የጎዳና ላይ ሩጫ፣ የማራቶን እና የሀገር አቋራጭ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አድርገዋል፡፡
በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ማራቶን ሚኪያሰ ባረጋ አንደኛ በመውጣት ሲያሸንፍ፤ አበባው ሙንየ 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል።
በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር በወንዶች ፈይሳ ቡሎ አሸናፊ ሲሆን፤ ገብሩ አብርሃ እና ጫላ ጉዴታ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን ጨርሰዋል።
በሴቶች ሃና መኮንን የድል ባለቤት ስትሆን፣ ማርታ ቦሬማ እና ሴና ተሰማ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡
በአቡዳቢ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር በወንዶች ሰውመሆን አንተነህ አንደኛ ሲወጣ፤ አባይነህ አየል ሁለተኛ ሆኖ ውድድሩን ማጠናቀቅ ችሏል።
በሴቶች ደግሞ አልማዝ ባራኪ 2ኛ እንዲሁም መግርቱ ሚዴቅሳ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።
በቻይና ሃንግዡ ማራቶን የሴቶች ውድድር ኩፍቱ ጣሂር አንደኛ በመውጣት ድል ተቀዳጅታለች።
በቱርክ የኢስታንቡል ማራቶን በሴቶች ውድድር ካሳነሸ አየነው አንደኛ በመውጣት ድል ስታስመዘግብ፣ አዝመራ አብርሃ 2ኛ እና ድርቤ ሂርቆ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።
በስፔን በተካሄደው የሴባስቲያን ሀገር አቋራጭ ውድድር ወገኔ አዲሱ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁን ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.