Fana: At a Speed of Life!

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2019 ኤፍ ኤም ሲ) ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል፡፡
በዛሬው ዕለት ነባር እና አዳዲስ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው እየገቡ ሲሆን፤ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ገብረሚካኤል ወልደገብርኤልን (ዶ/ር) ጨምሮ አመራሮች እና የተማሪዎች ሕብረት አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ተማሪዎችን የመቀበል ሂደት እስከ ነገ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚቀጥል ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲው በመግባት እንዲመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።
ከዚህ በተጨማሪ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ተማሪዎችን መቀበል የጀመረ ሲሆን፤ በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም የመማር ማስተማር ሥራቸውን እየጀመሩ ስለመሆናቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.