Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም (ኤፍ ኤም ሲ)ከጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቅቋል።

የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ፤ ጉባኤው በቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት፣ በወቅታዊ ችግሮች፣ በሀገር ሰላምና አንድነት፣ በሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት እንዲሁም የሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነት ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን ማስተላለፉ ተገልጿል።

እንዲሁም የሀገር ሰላም እና የሕዝብ አንድነትን አስመልክቶ በሰፊው ተወያይቶ ውሳኔም አሳልፏል።

በሌላ በኩል በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉዳት የደረሰባቸውን ምእመናን ታሳቢ በማድረግ፤ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦች እና በአጠቃላይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ድጋፍ ለማድረስ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሰብሳቢነት የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ መቋቋሙ ተመላክቷል።

በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.