Fana: At a Speed of Life!

የሐረር ከተማ የዓለም አቀፉ የሐር መንገድ የቱሪዝም ጥምረት አባል ሆነች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረር ከተማ የዓለም አቀፉ የሐር መንገድ የቱሪዝም ጥምረት አባል ሆናለች።
በቻይና ሉዣን ከተማ በተካሄደው የ2026 የሐር መንገድ የቱሪዝም ጥምረት አባል ከተሞች ዓመታዊ የጉዞ ኤጀንቶች ኮንፈረንስ ላይ የሐረር ከተማ የዚሁ ጥምረት አባል ሆና ተቀላቅላለች።
ይህ አባልነት ሐረር በዓለም አቀፍ የቱሪዝም መስክ የጎላ ትኩረት እንድታገኝ፣ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ጎብኚዎችን ለማስገባት፣ የታሪክና ባህል ቅርሶቿን በሰፊው ለማስተዋወቅ እንዲሁም ከጥምረቱ አባል ከተሞች ጋር በጋራ ለመሥራትና ልምድ ለመለዋወጥ ከፍተኛ ዕድል ይፈጥርላታል።
ከተማዋ ቀደም ሲልም የዓለም የቅርስ ከተሞች ድርጅት እና የዓለም የቱሪዝም ከተሞች ፌዴሬሽን አባል መሆኗ ይታወቃል።
ሐረር የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (UNESCO) በቋሚነት ያስመዘገበቻቸው የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ዓለም አቀፍ ቅርሶች ያሏት መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.