Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የጤና ሥርዓቷን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየሰራች ነው – ዶ/ር መቅደስ ዳባ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የጤና ሥርዓቷን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየሰራች ነው አሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፡፡
28ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።
ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በጤና ተቋማት ላይ በተሰራው ሪፎርም በሁሉም ሆስፒታሎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት እንዲኖር ተደርጓል፡፡
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ሁሉን አቀፍ የጤና ሥርዓቷን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየሰራች መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም በእናቶች ጤና ላይ በተሰራው ስራ የእናቶችን ሞት መቀነስ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
የወባ በሽታን ለመከላከል በተወሰደው ርምጃ 58 ከፍተኛ ጫና በነበረባቸው ወረዳዎች ላይ በተሰራ ስራ የሞት ምጣኔን ከ50 በመቶ መቀነስ እንደተቻለ አመልክተዋል፡፡
በቅድመ መከላከል ስራ የማህጸን ጫፍ ካንሰር በሽታን ለመከላከል በተደረገው ርብርብ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን የሚደርሱ ሴቶች የማህጸን ጫፍ ካንሰር ምርመራ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ጤናን ዲጂታላይዝ ለማድረግ በተያዘው ሀገራዊ ሪፎረም 226 የመንግሥት የጤና ተቋማት የካርድ ሥርዓታቸውን፣ 11 ሺህ የሚሆኑ የጤና ኬላዎች ደግሞ የመረጃ አያያዛቸውን ወደ ዲጂታል መቀየር መቻላቸውን አብራርተዋል፡፡
በጥላሁን ይልማ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.