ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከየኪሳራና ጉዳት ምላሽ ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር እና የኮፕ – 32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከየኪሳራና ጉዳት ምላሽ ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ኢብራሂማ ቼይክ ዲዮንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከኮፕ – 31 ጉባኤ ጎን ለጎን ነው የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉት፡፡
ውይይታቸው በጋራ የአየር ንብረትና የዘላቂ ልማት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ዙሪያ ትብብርን በማጠናከርና አዳዲስ የጋራ የሥራ ዕድሎችን በማሰስ ላይ ያተኮረ እንደነበር ነው የተገለጸው።
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከሚካሄደው ኮፕ – 32 በፊት አጋርነትን ለማጠናከርና የጋራ ጥረቶችን ለማስቀጠል ሐሳብ መለዋወጣቸው ተመላክቷል።