Fana: At a Speed of Life!

ቃላችንን በተግባር ለማረጋገጥ ቀን ከሌት እየተጋን እንገኛለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ቃላችንን በተግባር ለማረጋገጥ ቀን ከሌት ያለ እረፍት እየተጋን እንገኛለን አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአምስት ዓመታት ውስጥ ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ ለሕዝባችን ቃል ገብተናል ብለዋል።

ይህንንም ቃላችንን በተግባር ለማረጋገጥ ቀን ከሌት ያለ እረፍት እየተጋን እንገኛለን ሲሉ ገልጸዋል።

ሕዝባችን በመኖሪያ ቤት እጥረት ምክንያት የሚገጥመውን ፈተናና ስጋት በሚገባ እንረዳለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ደረጃቸውን የጠበቁና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ መኖሪያ ቤቶችን ማመቻቸት የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን፣ ለዜጎቻችን ያለብን አደራና ኃላፊነት መሆኑንም ጠንቅቀን እንገነዘባለን ነው ያሉት።

ዋነኛ ትኩረታችን ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ፣ የሕዝባችንን የመኖሪያ ቤት ጫና ማቃለል እና በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ ቤተሰቦች የተሻለ የኑሮ ምዕራፍ መክፈት እንደሆነም አመልክተዋል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.