አዲሱን ትውልድ ለላቀ ድል እንዲተጋ ማነሳሳታችሁን ቀጥሉ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ በክብር ከፍ አድርጋችሁ ማውለብለባችሁን እንዲሁም አዲሱን ትውልድ ለላቀ ድል እንዲተጋ ማነሳሳታችሁን ቀጥሉ አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ለወጣት ኢትዮጵያውያን አትሌቶቻችን በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው የ2026 የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ላስመዘገቡት አስደናቂና ታሪካዊ ድል ከልብ የመነጨ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቴን ላስተላልፍ እወዳለሁ ብለዋል።
5 የወርቅ እና 3 የብር ሜዳሊያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 8 ሜዳሊያዎችን በማግኘት የአትሌቲክስ የሜዳሊያ ሰንጠረዡን በ1ኛነት መምራታቸው ጠቅሰው፤ የኢትዮጵያን ጥልቅ የስፖርት ተሰጥኦ እና በአትሌቲክሱ ዘርፍ ያላትን ታላቅነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በክብር ከፍ አድርጋችሁ ማውለብለባችሁን እንዲሁም አዲሱን ትውልድ ለላቀ ድል እንዲተጋ ማነሳሳታችሁን ቀጥሉ ሲሉ የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።