Fana: At a Speed of Life!

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የኮፕ29 ፕሬዚዳንት ከነበሩት ሙክታር ባባዬቭ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የኮፕ32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአዘርባጃን ፕሬዚዳንት የአየር ንብረት ጉዳዮች ልዩ ተወካይና የኮፕ29 ፕሬዚዳንት ከነበሩት ሙክታር ባባዬቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የሁለቱን ሀገራት ትብብርና የልምድ ልውውጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን 32ኛውን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ32) ሀሳብ የተለዋወጡ ሲሆን፤ ልዩ ተወካዩ ሀገራቸው ለጉባኤው ዝግጅት ድጋፍ እንድምታደርግ አረጋግጠዋል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ መሪዎች አሿሿም የወጣቶች ተሳትፎና የአሠራር እቅድ ዝግጅትን ጨምሮ በኮፕ29 ፕሬዚዳንትነት ወቅት ያካበቱትን የቴክኒክ እውቀት፣ የአፈጻጸም ልምድና የተገኙ ተሞክሮዎች ለማካፈል ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.