Fana: At a Speed of Life!

የልማት ትልቁ ትርጉም በዜጎች ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የልማት ትልቁ ትርጉም በዜጎች ዕለታዊ ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፤ ትናንት ያስመረቅነው የኮሪደር ልማት የከተማችንን መሠረተ ልማቶች በማገናኘትና የመንገድ ኔትወርካችንን በማስፋት ከተማችንን የበለጠ ምቹና ለኑሮ ተስማሚ ከማድረጉም በላይ ለዜጎች ቀጥተኛ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ጥቅም አስገኝቷል።

ከ3 ሺህ 118 በላይ ሱቆች ታድሰውና አዳዲስ ተገንብተው፣ ከ491 በላይ የመኖሪያ ሕንፃዎችም መታደሳቸውንም ጠቁመዋል።

ይህም ለነጋዴዎች የተሻለ የንግድ አካባቢና የገቢ ዕድል፣ ለሥራ ፈላጊዎች ከፍተኛ የሥራ ዕድል፣ ለነዋሪዎች ደግሞ የተሻለ የመኖሪያ አካባቢ፣ ምቹ የእንቅስቃሴ ሁኔታና የተሻለ የኑሮ ጥራት መፍጠሩንም አመልክተዋል።

ለዚህ ውጤት መመዝገብ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ሥራውን ያስተባበሩ የከተማው አመራሮችና ሠራተኞች፣ ከጉልበት ሠራተኞች እስከ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎችና ሌሎች ተሳታፊዎች ላደረጉት ትጋትና አስተዋፅኦ አመስግነዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.