ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ከ5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ ጎን ለጎን ከፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
የቆየውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እና የጋራ ጥቅም ባላቸው ዘርፎች ላይ ትብብራችንን ማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረናል ብለዋል።