Fana: At a Speed of Life!

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የዓለም አቀፍ ትብብር ተጠባባቂ ሚኒስትር አምባሳደር ሴሲሊያ አዴንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ የሁለቱን ሀገራት ጠንካራ ወዳጅነት በማውሳት ግንኙነታቸውን ይበልጥ ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ መጪውን የደቡብ ሱዳን ምርጫ ሂደት በቅርበት እየተከታተለች እንደምትገኝ ገልጸው፤ የምርጫ ሂደቱን ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡

አምባሳደር አዴንግ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሰላምና ደህንነት የምታደርገውን ድጋፍ አድንቀው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግሥት ለደቡብ ሱዳናውያን ተማሪዎች ለሚያደርገው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.