የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የአብሮነት ቀንን በተለያዩ ሆስፒታሎች ከሚገኙ የህክምና ባለሞያዎች ጋር አሳለፉ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የአብሮነት ቀንን በተለያዩ ሆስፒታሎች በኮቪድ-19 የለይቶ ማከሚያ ማዕከላት ከሚገኙ የህክምና ባለሞያዎችን እና ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች ጋር አሳልፈዋል።
በዚህም ሃላፊዎቹ በሚሊኒየም የኮቪድ 19 የህክምና ማዕከል ፣በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ፣በአማኑኔል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል፣ በራስ ደስታ ሆስፒታል፣ በኤካ ኮተቤ እና በአለርት ህክምና ማዕከል በመገኘት በልዩ ልዩ የህክምና ክፍል ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙትን የህክምና ባለሞያዎችን እና ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች ጋር የአብሮነትን ቀን አሳልፈዋል።
የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በየሆስፒታሎቹ የኮቪድ-19 የለይቶ ማከሚያ ማዕከላት የጎበኙ ሲሆን÷ ለጤና ባለሞያዎች ያላቸውን አክብሮት እና አድናቆታቸውንም ገልፀዋል።
አብሮነታችንን ለኮቪድ-19 ታማሚዎች በማሳየት የሞያ ስነ-ምግባራችንን በማክበር ይህንን ወረርሽኝ በመተባበር ክንድ እንድናሸንፈው ትልቅ አቅም ይሆንልና ሲሉ የመስሪቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተናግረዋል።
አብሮነት የአንድ ቀን ሂደት ሳይሆን በተለይ የጤና ባለሞያዎች የሁልግዜ ተግባራችን መሆኑን በማሳየት ለሀገራቸችን እና ለህዝባችን በዚህ ፈታኝ ጊዜ ከፊት በመሰለፍ የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል አቅማችንን ያሳድግልናልም ብለዋል።
ህብረተሰቡ ራሱንና ቤተሰቡን ከኮሮና ቫይረስ እንዲከላከል እና የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡት ምክር እንዲተገብር የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጥሪ ማቅረባቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።