Fana: At a Speed of Life!

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለ1 ሺህ 29 የአየር ኃይል መኮንኖች የማእረግ እድገት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለ1 ሺህ 29 የአየር ኃይል መኮንኖች የማእረግ እድገት ሰጠ።

የማእረግ እድገቱን የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ ሰጥተዋል።

በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ÷ የማእረግ እድገቱ ለተጨማሪ ኃላፊነት የሚጋብዝ በመሆኑ መኮንኖቹ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በእለቱ የአየር ኃይል ከፍተኛ አመራሮችን ሀብት ማስመዝገብ፣ የተቋሙ የድረ ገፅ ምርቃት እና የአብራሪዎች ትጥቅ ትውውቅ ተደርጓል።

በዝግጅቱ ላይ የሰራዊቱ አባላት “ለገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶች የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመስጠት ቃል መግባታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.