Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ60 ሺህ አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 60 ሺህ 784 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 14 ሺህ 815 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 136
ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

በዚህም መሰረት በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 60 ሺህ 784 መድረሱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ከዚህ ባለፈ የ16 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 949 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 888 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 22 ሺህ 677 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 78 ሺህ 269 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 60 ሺህ 784 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 37 ሺህ 156 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 307 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 22 ሺህ 677 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ949 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን
በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.