አሜሪካ 2 ሺህ 200 ወታደሮቿን ከኢራቅ ልታስወጣ ነው
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካ እስከ መስከረም ወር መጨረሻ ድረስ 2 ሺህ 200 ወታደሮቿን ከኢራቅ ልታስወጣ መሆኑን አስታወቀች፡፡
በኢራቅ 5 ሺህ 200 ወታደሮች ሲኖሩ አሁን አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ወታደሮች ናቸው ከኢራቅ ይወጣሉ የተባለው፡፡
ቀሪዎቹ ወታደሮች ለኢራቅ የጸጥታ ዘርፍን ድጋፍ እያደረጉ እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ2016 የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በተለያዩ ሀገራት ያሉ ወታደሮች ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ባለፈው ወርም ወታደሮቹ በተቻለው ፍጥነት ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል በታህሳስ ወር የኢራኑ ጀነራል ቃሲም ሱለይማኒ ባግዳድ ላይ በድሮን መገደላቸውን ተከትሎ የኢራቅ ፓርላማ የውጭ አገር ወታደሮች በሀገራቸው የሚያካሂዱትን ተልዕኮ እንዲያበቃ ውሳኔ ማሳለፋቸው የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ፦ቢቢሲ