በሱዳን የተከሰተው ጎርፍ በሀገሪቱ የሰብአዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል- ተመድ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሱዳን የተከሰተው ጎርፍ በሀገሪቱ የሰብአዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስጠነቀቀ።
በሀገሪቱ በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ ዝናብ የሚጠበቅ ሲሆን÷ ይህንን ተከትሎ በሱዳን የሰብዓዊ ቀውስ ሁኔታ እየተባባሰ እንደሚመጣ የተባበሩት መንግስታት አስጠንቅቋል ፡፡
ድርጅቱ አያይዞም ለችግሩ ምላሽ ለመስጠት የሚያስፈልጉ አቅርቦቶች እጥሪት እንዳለበት ገልጿል፡፡
ለሳምንታት የዘለቀው ከባድ ዝናብ ከአንዱ በስተቀር በ18ቱም የሱዳን ግዛቶች የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከትሏል፡፡
ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎች በአደጋው የተጎዱ ሲሆን÷ በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ተፈናቅለዋል ፡፡
ከዚያም ባለፈ በሳህል በርሃ አካባቢ በሚዘንበው ከባድ ዝናብም የጎርፍ መጥለቅለቅ እየተከሰተ መሆኑ ተነግሯል ፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።