ዩክሬን ውስጥ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የ22 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዩክሬን በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የ22 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡
አንቶኖቭ-26 የተባለው የጦር አውሮፕላን የመከስከስ አደጋ ያጋጠመው በምስራቃዊ ዩክሬን ከተማ ለማረፍ በተቃረበበት ወቅት ነበር ተብሏል።
በአውሮፕላኑ 27 ሰዎች ተሳፍረው የነበረ ሲሆን 22ቱ መሞታቸው ሲረጋገጥ ሁለት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡
ሶስቱ ሰዎች ደግሞ የጠፉ ሲሆን እነሱን ለማግኘት ፍለጋው ቀጥሏል ነው የተባለው፡፡
አውሮፕላኑ ከአገሪቱ አየር ኃይል አየር ማረፊያ መነሳቱ እና የልምምድ በረራ እንደነበረም ታውቋል፡፡
ከሟቾቹ መካከል አብዛኛዎቹ ሰልጣኝ አብራሪዎች መሆናቸውን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የአደጋው መንስኤም በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ነው የተገለፀው፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ