የሱዳን ባለሃብቶች የልዑካን ቡድን በምዕራብ አርሲ ዞን ጉብኝት አደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሱዳን ባለሃብቶች የልዑካን ቡድን በዛሬው እለት በምዕራብ አርሲ ዞን ጉብኝት አድርጓል፡፡
ልዑኩ ዛሬ በዞኑ የሚገኙ የአብጃታ ሻላ ብሔራዊ ፓርክና የላንጋኖ ሐይቅ መጎብኘቱን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡
ቀደም ባለው ቀንም በቢሾፍቱ የሚገኙ ሪዞርቶችን መጎብኘቱ ይታወሳል፡፡
የኦሮሞያ ክልል ቆይታውን ካጠናቀቀ በኋላም ከገበታ ለሀገር ኢንቨስትመንት ጋር የሚተሳሰር ልማት ሥራ ላይ ለመሳተፍ አርባምንጭ ከተማ ገብቷል።
የልዑካን ቡድኑ አርባምንጭ ከተማ ሲገባ የጋሞ ዞን፣ የአርባምንጭ ከተማ እና የአርባምንጭ ዙሪያ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።
30 የሚሆኑ የሱዳን ባለሀብቶችን ከኩሪፍቱ ሪዞርት ጋር በመተባበር ከገበታ ለሀገር ኢንቨስትመንት ጋር የሚተሳሰር ልማት ሥራ ላይ ለመሳተፍ ነው አርባምንጭ ከተማ የገቡት፡፡
ባለሀብቶቹ በዞኑ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ከጎበኙ በኋላ ለማልማት ፍለጎታቸውን ያሳያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጋሞ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡