Fana: At a Speed of Life!

በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ለ3 ነጥብ 3 ሚሊየን የከተማ መሬቶች ይዞታ የመመዝገብ እና የማረጋጋጥ ስራ ለማከናወን ታቅዷል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ለ3 ነጥብ 3 ሚሊየን የከተማ መሬቶች ይዞታ የመመዝገብ እና የማረጋጋጥ ስራ ለማከናወንማቀዱን የፌደራል ከተማ መሬት እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጄንሲ አስታወቀ፡፡

የፌደራል ከተማ መሬት እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጄንሲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀው ÷ በቀጣይ 5 ዓመታት 7 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች በካዳስተር ስርዓት ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ይሰራል፡፡

የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ሃላፊ አቶ አራጌ ክብረት ÷ የካዳስተር ስርዓቱ በአራቱ ዋና ዋና ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይ 5 ዓመታትም በ60 ከተሞች ላይ የካዳስተር ምዝገባ ተቋማት ወደ ስራ እንደሚገቡ ጠቅሰው÷ በተያዘው ዓመትም 350 ሺህ ይዞታዎችን ለመመዝገብ እና ለማረጋገጥ መታቀዱን ጠቁመዋል፡፡

ቀሪዎቹን ክልሎች ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ነው ያሉት ሃላፊው÷ የካዳስተር ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግም ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.