Fana: At a Speed of Life!

በቀጣዩ ዓመት የሚከበረውን 34ኛውን የአለም ቱሪዝም ቀን የሲዳማ ክልል እንደሚያዘጋጅ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱማሌ ክልል ላለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ሲከበር የቆየው 33ኛው የአለም ቱሪዝም ቀን ተጠናቋል።
 
የአለም ቱሪዝም ቀን ˝ቱሪዝም ለገጠር ልማት˝ በሚል መሪ ቃል በጅግጅጋ ከተማ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች የተከበረ ሲሆን በወቅት የክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።
 
የማጠቃላይ ስነ ስርዓቱም በጅግጅጋ በተካሄደበት ወቅት በ2014 የሚከበረውን የአለም ቱሪዝም ቀን የሲዳማ ክልል እነዲያዘጋጅ መወሰኑን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
በዝግጅቱ ላይ የብሄር ብሄረሰቦች የባህላዊ አለባበስ ትርኢቶችና የኪነ ጥበብ ስራዎች ቀርበዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.