የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ በፕሮፌሰር መስፍን ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።
ርዕሰ መስተዳድሩ ፕሮፌሰር መስፍን ትልቅ የእውቀት አባት፣ ቁርጠኛ ሰላማዊ ታጋይ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ላመኑበት ጉዳይ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ወደኋላ የማይሉ የጽናት ተምሳሌትና የአዲሱ ትውልድ አርአያ ናቸው ብለዋል፡፡
ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለአድናቂዎቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡