Fana: At a Speed of Life!

በዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 34 ሚሊየንን ተሻገረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ34 ሚሊየን አልፏል፡፡

በዓለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ከ34 ሚሊየን 162 ሺህ በላይ ደርሷል፡፡

በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም ከ1 ሚሊየን 18 ሺህ በላይ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

በአንጻሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ25 ሚሊየን 433 ሺህ በላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡

አሜሪካ፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ እና ኮሎምቢያ ቫይረሱ ከጸናባቸው ሃገራት ቀዳሚ በመሆን ከአንድ እስከ አምስተኛ ደረጃ ተቀምጠዋል፡፡

ምንጭ፡- ዎርልድ ኦ ሜትር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.