Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ዜጎች የተከሏቸውን ችግኞች እንዲንከባከቡ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዜጎች የተከሏቸውን ችግኞች እንዲንከባከቡ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባሳለፍነው የአረንጓዴ ዐሻራ ወቅት የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ ላይ ለሚገኙት ሁሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ባለፈው ዓመት ተተክለው ከጸደቁ ችግኞች የተሻለ የጽድቀት መጠን እንዲገኝም ሁሉም የተከላቸውን ችግኞች እንዲንከባከብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በ2011 ዓ.ም በአረንጋዴ አሻራ 4 ቢሊየን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን በ2012 ዓ.ም ደግሞ 5 ቢሊየን ችግኞች ተተክለዋል፡፡

በአምስት አመታት ውስጥም 20 ቢሊየን ችግኞችን የመትከል እቅድ ተይዟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.