የትግራይ ልማት ማህበር 5 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የኮቪድ 19 መመርመሪያ ኪቶችን ለትግራይ ክልል ጤና ቢሮ አስረከበ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ልማት ማህበር 5 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የኮቪድ 19 መመርመሪያ ኪቶችን ለትግራይ ክልል ጤና ቢሮ አስረከበ፡፡
ድጋፉን የትግራይ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አክሊሉ ሃይለሚካኤል ለትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ ዶክተር ሪኧ ኢሳያስ አስረክበዋል፡፡
ድጋፉ በክልሉ ያለውን የኮቪድ19 መመርመሪያ ቁሳቁስ እጥረት ለመቅረፍ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
የትግራይ ልማት ማህበር ከዚህ ቀደም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የተለያዩ ድጋፎች ማድረጉን በርክክብ ስነ ስርአቱ ወቅት ተገልጿል፡፡