የሶሚሊያው ፕሬዚዳንት መሀመድ ፎርማጆ አስመራ ገቡ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፎርማጆ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ኤርትራ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንት የሁለት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ አስመራ ሲገቡ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በጉብኝቱም የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በሁለትዮሽ ግንኙነትታቸው ላይ እየታየ በሚገኘው መሻሻል እና ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።
በተመሳሳይ በቀጠናዊ ልማቶች እና ለውጦች ዙሪያ የሚወያዩ ሲሆን ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፎርማጆ የተለያዩ የልማት ስራዎች እና ፕሮጀክቶችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።