Fana: At a Speed of Life!

የብሔር ብሔረሰቦች በዓል በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የአከባበር ለውጥ ተደረገበት

አዲስ አበባ ፣መስከረም 25 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት በዘንድሮው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የአከባበር ለውጥ እንደተደረገበት አስታወቀ፡፡

ከዚህ ቀደም በአንድ ክልል አዘጋጅነት የሚከበርበት መንገድ ቀርቶ ከኅዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በወጣ መርሀ ግብር በየክልሉ እንደሚከበርም ነው ያስታወቀው፡፡

ይህን ተከትሎም ኅዳር 15 በትግራይ፣ ኅዳር 16 በደቡብ፣ ኅዳር 17 በሶማሌ፣ ኅዳር 18 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ኅዳር 19 በአማራ፣ ኅዳር 20 በአዲስ አበባ፣ ኅዳር 21 በሐረር፣ ኅዳር 22 በጋምቤላ፣ ኅዳር 23 በአፋር፣ ኅዳር 24 በኦሮሚያ እና ኅዳር 25 በሲዳማ ይከበራልም ነው ያለው።

የሕዝብ አንድነትና ትብብርን ለመፍጠር ዓላማ አድርጎ በሚከበረው በዚህ በዓል ላይ የተለያዩ ማኅበራዊ ተግባራት ይከናወናሉም ነው የተባለው።

ኢትዮጵያውያን በደም የተሳሰሩ መሆኑን ለማመልከት የአንዱ ክልል ወደ ሌላ ክልል በመሄድ ደም መለገስ ከሚከወኑ ተግባራት መካከል አንዱ መሆኑም ተጠቅሷል።

የክብረ በዓሉ አካል የሆነ ችቦም በሁሉም ክልሎች እንደሚዘዋወር መገለጹንም ኢቢሲ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.