በሲያትል የኮሮና ቫይረስ ግብረ ሃይል እና በሲያትል የሚገኙ ወገኖች 200 ሺህ ዶላር የሚገመቱ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን አበረከቱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሲያትል የኮሮና ቫይረስ ግብረ ሃይል እና በሲያትል የሚገኙ ወገኖች 200 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚገመቱ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ እና ሌሎች የሕክምና ቁሳቁሶችን ለጤና ሚኒስቴር አበረከቱ፡፡
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ድጋፉን ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ጋር በመተባበር ቁሳቁሶቹን ያለክፍያ ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገባ ስላደረገም አመስግነዋል፡፡
ቦይንግ ከትናንት በስቲያ ከ9 ሺህ 71 ኪሎ ግራም በላይ የህክምና ቁሳቁሶች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር ያለ ክፍያ ማጓጓዙ ይታወሳል፡፡
ከዚህ ቀደምም በአሜሪካ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ወገኖች የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡