ተጨማሪ 618 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 956 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ6 ሺህ 62 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 618 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሯ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ 292 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም 956 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 34 ሺህ 16 ደርሷል፡፡
ባለፉት 24 ሰአታት የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 1 ሺህ 230 መድረሱን ገልጸዋል፡፡
እስካሁን በኢትዮጵያ ለ1 ሚሊየን 307 ሺህ 632 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 79 ሺህ 437 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ ቁጥር 34 ሺህ 16ቱ ከቫይረሱ ሲያገግሙ 44 ሺህ 189 ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ አለባቸው፡፡