Fana: At a Speed of Life!

ሁሉን አቀፍ ሃገራዊ ምክክር ኢኒሼቲቭ በይፋ ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሁሉን አቀፍ ሃገራዊ ምክክር ኢኒሼቲቭ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመስርቷል፡፡

ኢኒሼቲቩ መሰረታዊ በሆኑ ሃገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዘላቂ የምክክር መድረክን የመፍጠር ትልም እንዳለ ነው የተገለጸው፡፡

በኢኒሼቲቩ ይፋዊ ምስረታ ላይ ንግግር ያደረጉት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሙሳ አደም፣ ኢኒሼቲቩ ሃገሪቱ የሚያስፈልጋትን የተቀናጀ ብሄራዊ ምክክር እውን ለማድረግ ከፍ ያለ ሚና እንዳለው ነው ያብራሩት፡፡

ብሄራዊ የምክክር ሂደቱ የሃሳብ ልዩነቶችን ደረጃ በደረጃ ከማቀራረብ ባሻገር፣ በተሳታፊዎች መካከል መልካም ግንኙነትንና የአንድ ሃገር ልጅነትን መንፈስ የሚያጎለብቱ አሰራሮችን እንደሚከተልም ተናግረዋል፡፡

የምክክሩ ተሳታፊዎች ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ፣ እንዲሁም ሁሉንም ክልሎች ያሳተፈ እንዲሆን ይሰራል ተብሏል፡፡

ዴስቲኒ ኢትዮጵያ፣ የሃሳብ ማዕድ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የመሰረቱት ይህ ሃገራዊ የምክክር አውድ፣ በ2 ወራቶች ውስጥ ወደ ስራ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

 

በአወል አበራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.