Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋን የትራንስፖርት ችግርን ለመፍታት 560 አውቶብሶች በኪራይ ወደ ስምሪት ሊገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የትራንስፖርት ችግርን ለመፍታት 560 አውቶብሶች በኪራይ ወደ ስምሪት እንዲገቡ መሰኑን አስታወቀ፡፡
 
ካቢኔው ዛሬ ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው በህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦት እና ፍላጎት መካከል የሚታየውን የነዋሪዎች አቤቱታ እና እንግልት ለመፍታት በቀረበ አማራጭ ሃሳቦች ዙሪያ በተወያየበት ወቅት ነው ውሳኔውን ያሳለፈው፡፡
 
በከተማዋ በህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦትና ፍላጎት መካከል የሚታየውን ክፍተት ለሟሟላት የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ሁኔታ ተጨማሪ አውቶብሶችን በኪራይ ወደ ስምሪት በማስገባት የነዋሪውን ቅሬታ መፍታት አስፈላጊ በመሆኑ ውሳኔው ማሳለፉ ገልጻል።
 
አስተዳደሩ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከመንገድ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ጀምሮ ተጨማሪ 500 የአውቶብስ ግዢ በሂደት ላይ እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡
 
በተጨማሪም 125 አውቶብሶች እድሳት ተደርጎላቸው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ መሰደረጉንም ገልጸዋል፡፡
 
የትራንስፖርት ችግሩን በጊዜያዊነት ለመፍታት ውሣኔውን በአፋጣኝ እንዲፈጸም እና የአውቶብሶቹ የኪራይ ውል እና ተያያዥ የአፈፃፀም መመሪያዎች በአንድ ሣምንት ጊዜ እንዲጠናቀቅም ካቢኔው አቅጣጫ ማስቀመጡንም ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.