አቶ ልደቱ አያሌው ላይ ሌላ ክስ ቀረበባቸው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ልደቱ አያሌው ላይ ከህገ መንግስት ውጪ ህገመንግስቱን በማፍረስ የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነድ በማዘጋጀት በሚል ሌላ ክስ ቀረበባቸው፡፡
ክሱን ያቀረበው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሲሆን÷ ክሱም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ተዘዋዋሪ ምድብ ችሎት ነው፡፡
ችሎቱም የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመመልከት ለጥቅምት 5 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም ክስ በተመሰረተባቸው በህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ላይ ምስክር ለመስማት ለጥቅምት 3 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በታሪክ አዱኛ