ከ5 ሳተላይቶች ከፍተኛ ጥራት ያለው መረጃ የሚቀበለው የምድር ሳተላይት መቀበያ ጣቢያ ግንባታ 50 በመቶ ደረሰ
አዲስ አበባ ፣መስከረም 28 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከአምስት ሳተላይቶች ጥራት (ሪዞሉሽን) ያለው መረጃ የሚቀበል የምድር ሳተላይት መቀበያ ጣቢያ ግንባታ 50 በመቶ መድረሱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለፀ።
ግንባታው ሲጠናቀቅ የውጭ ምንዛሪ ከማዳን ባሻገር ለተለያዩ አገሮች የሳተላይት መረጃ መሸጥ ያስችላል ተብሏል።
በቴክኖሎጂ፣ በኢኖቬሽንና ዲጅታላይዜሽን አማካኝነት ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድገው የፖሊሲ ክለሳ የተጠናቀቀ ሲሆን ዓዋጆችም እየተዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ባከናወናቸው ተግባራት ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሲሳይ ቶላ እንዳሉት ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የያዘውን ራዕይ በቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና ዲጅታላይዜሽን መሰረተ ልማት መታገዝ አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።